09Sport
በቻን ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ጋር የተደለደለችው ኤርትራ ጨዋታዎቹን እንደማታከናውን አሳውቃለች። የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የደርሶ መልስ ጨዋታዎች በደቡብ ሱዳን ጁባ ስታዲየም እንደሚደረጉ በሁለቱ ሀገራት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች መግባባት ላይ ተደርሶ የነበረ ሲሆን ከደቂቃዎች በፊት በተሰማ መረጃ ኤርትራ ከማጣሪያው ጨዋታ ራሷን ማግለሏ ታውቋል።
ይህንን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በወጣለት መርሐ-ግብር ከታንዛኒያ እና ሱዳን አሸናፊ ጋር ቀጣይ መርሐ-ግብሩን የሚከውን ይሆናል።